
ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ትኬትዎን ከኢንተርኔት ላይ ይቁረጡ
በኢትዮጵያ የጉዞ ወኪሎች ውስጥ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የጉዞ ምዝገባና ትኬትን በኢንተርኔት ላይ ለመግዛት የሚያስችለው ድህረ ገጽ (ወብ ሳይት) www.yebbo.com ስራውን ጀመረ፡፡ ላለፉት ብዙ አመታት ከአሜሪካ አህጉር ወደ ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ደንበኞቱን ሲያገለግል የቆየው፣ የቦ የጉዞ ወኪል ከደንበኞቹ የሚቀርቡለትን አስተያዮቶች እን ጥቆማዎች እንዲሁም በአሜሪን ውስጥ ያለውን የግዜ እጥረት ከሚዛን ውስጥ በማስገባትና በመገንዘብ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን በማስፋፋት በአሜሪካ እና በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በለጠ ለማገልገል ባለው የረጅም ጊዜ እቅድ መሰረት እንሆ በኢትዮጵያ ጉዞ ወኪሎች ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን በኢንተርኔት ላይ ትኬት መቁረጥ የሚያስችለውን ድህረ ገፅ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ይህ ድህረ ገፅ ለኢትዮጵያዊያን እና ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ደንበኞቹ ታስቦ የተነደፈ ሲሆን፣
በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ከሚሆኑት አየር መንገዶች ውስጥ አንዱ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) በተቀዳሚነት እንዲታይ እና መንገዶኞቻችን በይበልጥ የሀገራችንን አየር መንገድ እንዲጠቀሙ በማሰብ ቅድሚያ የተሰጠው ሲሆን፣ ሌሎችም እንደ ብሪትሽ አየር መንገድ (British Airways) ሉፍታንዛ (Lufthansa) እና ቨርጂን (Virgin Airlines) እና ኬኤልኤም(KLM) የመሳሰሉት አየር መንገዶችንም ያቀፈ ነው፡፡
ባሁኑ ወቅት የቦ የጉዞ ወኪል ወብ ሳይት ለደንበኞቹ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን ክፍት ሲሆን፣ ማናኛውም ተሳፋሪ የክሬዲት ካርድ (credit card) እና ኢንተርኔት (internet) መስመር ማግኘት እስከቻለ ድረስ ካለምንም እንከን ጉዞውን ከሞቀ ቤቱ ቁጭ ብሎ በፈለገው መልክና የተስማማውን ዋጋ እራሱ መርጦ ትኬቱን መግዛት ሲችል፣ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሮኒክ ትኬትን (Electronics Ticket/e_ticket) መጠቀም ሲጀምር አንድ ተሳፋሪ ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትኬቱን መቁረጥ እና የቀረውን ጊዜ ለሌላ ነገር ማዋል ይችላል ይችል፡፡ እንዲሁም በብዛት ተሳፋሪዎች ዋጋ ለማዋቅ ከተሌዪ የጉዞዎኪሎች በመደወል የሚያተፉትን ጊዜ ይቆጥባል፡፡
እንዲሁም በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ሀገሮች ያሉ ተሳፋሪዎች የሃገር ውስጥ በረራ ትኬት መቁረጥ ከፈለጉ ከወብሳይታችን ላይ ከታዋቂ የኢንተርኔት የጉµ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ስመሰረትን በድህረ ገፃችን ላይ በመሄድ መቁረጥ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አውሮፕላን፣ መኪናና ሆቴል አሜሪንና አውሮፓ ለመከራየት ከ ኦርቢትስ (Orbitz.com)፣ ከኤክስፒድያ (Expidia.com) እና ቺፕትኬትስ (Cheaptickets.com) ከተባሉ ድርጅቶት ጋር ግንኙነት ስላለን የሀገር ውስጥ በረራዎችን ከድህረ ገፃችን ላይ ጎራ በማለት መቁረጥ ትችላላችሁ፡፡
ለወደፊቱም የቦ የጉµ ወኪል የደንበኞቻችን ጊዚ ለመቆጠብ ተጓዡ በተመቸው ቀንና ሰዓት የመኪና፣ የሆቴልና የባቡር መከራዬትን የሚያስችል ድህረ ገፅ ለማቅረብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከቢሯችን ጎራ ቢሉ ወይም ከወብሳይታችን www.yebbo.com ቢሄዱ የፓስፖረት ማመልከቻ ፎርም እንዲሁም ሰለ ጉዝዎ ከሀገር ውስጥ ሰለተሰጡ የጉዞ ማሳሰቢያወችን/ማስጠንቀቂያወ (Travel Warnings and advisories)ማንበብ ሲችሉ፣ ከቢሯችን በመምጣት ደግሞ የፓስፖረት ፎቶ፣ የትርጉም ስራ፣ የኖቶሪ ኅትመት (Notary Public) የማድረግ አገልግሎት ሲኖረን፣ የፋክስ ማድረግ የኢሜል እና የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎችንም የመስጠት አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
በበለጠ ለመረዳት እባክዎ ዛሬ ነገ ሳይሉ ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ እንዲሁም የእርስዎ አስተያየትም ሆነ ጥቆማ አገልግሎታችንን ለማሻሻል ስለሚጠቅሙን እባክዎ በ info@yebbo.com ይፃፉልን፡፡
www.yebbo.com
The Number #1 Ethiopian Travel Web site